News Archive

04 Feb 2025

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘብ ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ደረሰ፡፡

በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተሰበሰበው ተቀማጭ ገንዘብ 58.3 በመቶ መሰብሰብ ችሏል፡፡

04 Feb 2025

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሰባት ወራት ከ303 ቢልዮን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ አሰባሰበ።

በባንኩ ታሪክ የተመዘገበ ትልቁ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን በመሆን ተመዝግቧል።

27 Jan 2025

የውጭ ሀገራት ገንዘብ ምንዛሬ ዋጋን በገበያ እንዲወሰን የሚያደርግ ፖሊሲ ወደ ስራ ከማስገባት በፊት የተወሰዱ የእርምት እርምጃዎች ገበያውን ለማረጋጋት እንዳገዙ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ተናገሩ፡፡

አዲስ ፖሊሲ ሲተገበር የራሱ መልካም ውጤት ይዞ እንደሚመጣ ሁሉ የጎንዮሽ ጉዳትም ይጠበቃል ያሉት አቶ አቤ ይህንን ሪፎርም ጉዳቱን በመቀነስ ጠቀሜታዉን ከፍ ለማድረግ የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶች ተደርገው ተተግብሯል ብለዋል፡፡

27 Jan 2025

የገንዘብ አጠቃቀም በሥርዓት እንዲመራ መደረጉ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም ውጤታማ እንዲሆን እንዳስቻለ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ገለጹ።

የውጭ ሀገራት ገንዘብ እጥረትን ለመቅረፍ ተጨማሪ ገንዘብ ማተም የገበያውን እንቅስቃሴ የሚያዛባ እንደሆነ የገለፁት አቶ አቤ የገንዘብ አጠቃቀም በሕግና በሥርዓት እንዲመራ መደረጉ የውጭ ሀገራት ገንዘብ ዋጋ ተለዋዋጭ እንዳይሆን እና ገበያውን ለማረጋጋት አግዟል ብለዋል፡፡