የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቦርድና የማኔጅመንት አባላት እንዲሁም የባንካችን ሰራተኞች በሙሉ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በትላንትናዉ ዕለት በደረሰዉ ድንገተኛ የመሬት ናዳ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን የተሰማንን ልባዊ ኃዘን እየገለጽን በአደጋው ቤተሰቦቻቸውን እና ወዳጅ ዘመዶቻቸዉን ላጡ ወገኖቻችን እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መፅናናትን እንመኛለን።
ለአገራችን የኢኮኖሚ ዕድገት የድርሻቸውን ላበረከቱ ተቋማት እና አመራሮች ሽልማት የሚያበረክተው አቢሲኒያ የኢንዱስትሪ ሽልማት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት ለአቶ አቤ ሳኖ ለባንኩ ትርፋማነትና ስኬታማነት ባሳዩት ብቃት ያለው አመራር የ2016 ዓ.ም. የዳይመንድ ደረጃ ኒሻን እና ዕውቅና አበርክቶላቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደግሞ ከ75 ዓመታት በላይ አገርን በማገልገልና በተከታታይ ትርፋማና ስኬታማ በመሆኑ የዳይመንድ ደረጃ ልዩ ዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል፡፡
ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ዋና መ/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው የማህበሩ ቦታ ላይ የሚለማው ይኸው ሕንጻ ከ15.5 ቢሊየን ብር በላይ እንደሚፈጅ ተገምቷል፡፡ ስምምነቱን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚደንቱ አቶ አቤ ሳኖ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ደግሞ ፕሬዚደንቱ አቶ አበራ ቶላ ፈርመዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ በከፍተኛ አመራሮች ዘርፍ የዳይመንድ ደረጃ ኒሻን ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እሁድ ሐምሌ 14 ቀን 2016 ዓ/ም በኢንተርሌግዠሪ ሆቴል በተካሄደ ሥነ- ሥርዓት የአቢሲኒያ የኢንዱስትሪ ሽልማት የዳይመንድ ደረጃ ልዩ የዋንጫ ተሸላሚ መሆን ችሏል፡፡
ከ ሐምሌ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ2016 (2023/24) በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ጉባኤ የ2017 (2024/25) በጀት ዓመት ዕቅድ ግምገማ የቀጣይ በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ሐምሌ 14 ቀን 2016 ዓ/ም ተጠናቋል፡፡
CBE Noor is one of the full-fledged interest free banking services. Designed to comply with the central tenets of Sharia (or Islamic law) of doing business.
The core processes of the bank entrusted with the task of international banking services. The services are now provided at all branches of the bank with a single contact point of customer service relationship officers assigned for this purpose only.
Delivering banking services through high level of process automated machines and web-based. It provides easy, convenient, flexible and secure banking services for CBE customers using their digital cards, mobile phone, or internet accesses.
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ለባንኩ ትርፋማነትና ስኬታማነት ባሳዩት ብቃት ያለው አመራር የ2016 ዓ.ም. የዳይመንድ ደረጃ ኒሻን እና ዕውቅና ተበርክቶላቸዋል፡፡ በሽልማት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ በመገኘት ዕውቅናውንና ሽልማቱን የተረከቡት የባንኩ የሰው ኃይል ም/ፕሬዚዳንት አቶ ኤፍሬም መኩሪያ እና ሌሎችም የባንኩ ኃላፊዎች በፕሬዚዳንቱ ቢሮ በመገኘት ሽልማቱን ለአቶ አቤ ሳኖ አስረክበዋቸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚደንት አቶ አቤ ሳኖ በፊርማ ሥነ -ሥርዓቱ ላይ እንደተናገሩት ከ14.4 ቢሊየን ብር በላይ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል የሚሸፈን ሲሆን፤ ቀሪው 1.1 ቢሊየን ብር በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ይሸፈናል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ በከፍተኛ አመራሮች ዘርፍ የዳይመንድ ደረጃ ኒሻን ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም. በተፈጠረ ችግር ምክንያት ያለአግባብ ተወስዶ የነበረውን ገንዘብ በማስመለስ ሂደት የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የባንኩ ሠራተኞች፣ ዲስትሪክቶች እና ቅርንጫፎች፣ የመንግስት አካላት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የተቀማጭ ገንዘብ አሰባሰብ፣ የውጭ ምንዛሬ ግኝት እና ኢኮኖሚያዊ አዋጭነት (Economic Profitability) የዲስትሪክቶችን እና ቅርንጫፎችን የሥራ አፈፃፀም ለመመዘን የተቀመጡ መስፈርቶች ናቸው፡፡
ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም. በተፈጠረ ችግር ምክንያት ያለአግባብ ተወስዶ የነበረውን ገንዘብ ለማስመለስ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ሌት ቀን በትጋት ሙያዊ ኃላፊነታቸውን የተወጡ ሰባት የባንኩ ሠራተኞች ከባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ እጅ የምስክር ወረቀት እና ሽልማት ተቀበለዋል፡፡
Branchs
Customers
Partners
Transactions per Month