News Archive

10 Mar 2025

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 50 ሚሊዮን ብር ለነጋድራስ የፍፃሜ ተወዳዳሪዎች እንደሚያበድር ቃል ገባ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለእያንዳዳቸው 10 ሚሊዮን ብር ብድር ያለማስያዣ እንደሚሰጥ አስታውቋል።

10 Mar 2025

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲቢኢ ኑር የ1446ኛው ዓ.ሒ የረመዷን ፆምን ምክንያት በማድረግ በሻሸመኔ ከተማ ገቢና አጋዥ ለሌላቸው ሙስሊም የህበረተሰብ ክፍሎች ማዕድ አጋራ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሻሸመኔ ዲስትሪክ ዳይሬክተር አቶ ደዋኖ ሁሴን በመርሐ ግብሩ ላይ እንደተናገሩት ባንኩ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ከሚያደርገው ጥረት ጋር ተያይዞ በረመዷን ወር ለሙስሊሙ ማህበረሰብ አብሮነቱን ለማሳየት የማዕድ ማጋራቱ መከናወኑን ገልፀዋል።

10 Mar 2025

ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የ 3 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ!

ድጋፉን በራሳቸው እና በኮሜርሻል ኖሚኒስ ስም ያስረከቡት የኮሜሪሻል ኖሚኒስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኮማንደር ጥላሁን ፀጋዬ መቄዶንያ ለሚሠራው የበጎ አድራጎት ሥራ ያላቸውን አድናቆት ገልፀው፣ በቀጣይም አቅም በፈቀደ ሁሉ እገዛ ለማድረግ ቃል ገብተዋል፡፡

28 Feb 2025

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጠቃላይ ተቀማጭ 1.54 ትሪሊዮን ብር ደረሰ።

አቶ አቤ አጠቃላይ በባንኩ ከተፈጸሙ የገንዘብ ግብይቶች 84.5 በመቶ የሚሆነው በዲጂታል የክፍያ አማራጮች የተፈጸሙ መሆናቸውን ጠቅሰው ይህም አበረታች እንደሆነና የአገልግሎት ጥራቱንም ይበልጥ ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቶት እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።