News Archive

24 Jul 2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለአግባብ የተወሰደበትን ገንዘብ በማስመለስ ሂደት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ሠራተኞች፣ ዲስትሪክቶች እና ቅርንጫፎች እውቅናና ሽልማት ሰጠ፡፡

ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም. በተፈጠረ ችግር ምክንያት ያለአግባብ ተወስዶ የነበረውን ገንዘብ ለማስመለስ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ሌት ቀን በትጋት ሙያዊ ኃላፊነታቸውን የተወጡ ሰባት የባንኩ ሠራተኞች ከባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ እጅ የምስክር ወረቀት እና ሽልማት ተቀበለዋል፡፡

24 Jul 2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዓመታዊ ጉባኤ የቀጣይ በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተጠናቀቀ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሪዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ በጉባኤው ማጠቃለያ መልእክታቸው የባንኩን የቀጣይ ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች አመልክተዋል፡፡

24 Jul 2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 3.2 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ሰብስቧል፡፡

በ2023/24 በጀት ዓመት ከወጪ ንግድ 878.5 ሚሊዮን ዶላር ከውጭ ሃዋላ ደግሞ 2.07 ቢሊዮን ዶላር እንዲሁም በግዢ 286.1 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ግኝት በባንኩ ተሰብስቧል፡፡

24 Jul 2024

"ሎተሪ ደርሶዎታል" በማለት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስም የማታለል ወንጀል የፈፀሙ ግለሰቦች ተያዙ::

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስም ስልክ በመደወል የማታለል ወንጀል የፈፀሙ ግለሰቦች ተይዘው ምርመራ እየተጣራባቸው ነው፡፡