News Archive

27 Jul 2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አራት አትሌቶችን ለፓሪስ ኦሎምፒክ አስመረጠ።

በፈረንሳይ ሀገር በፓሪስ ከተማ 33ኛው የአሎምፒክ ውድድር ከ ሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ ለ15 ቀናት ይካሄዳል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም አራት አትሌቶችን በአትሌቲክስ እንዲወዳደሩ ማስመረጥ ችሏል፡፡ ለአትሌቶቹም የኢትዮጵያን እና የባንኩን ሰንደቅ ዓላማ በማበርከት የመልካም ምኞት አሸኛኘት አድርጎላቸዋል፡፡

27 Jul 2024

የሲቢኢ ብር ተጠቃሚዎች ቁጥር ከ11.7 ሚሊዮን በላይ ደረሰ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሰኔ 2009 ዓ.ም የሲቢኢ ብር አገልግሎትን እንደ አንድ የዲጂታል የባንክ አገልግሎት አማራጭ አድርጎ ጀምሯል፡፡ ባንኩ የሲቢኢ ብር አገልግሎቱን ለማሻሻል በየጊዜው በወሰዳችው እርምጃዎች በሞባይል መኒ አገልግሎት ያለውን የገበያ ድርሻ አጠናክሮ ለመቀጠል አስችሎታል፡፡ ሲቢኢ ብር ፕላስ (CBEBirr Plus) በሚል በአዲስ መልክ አሻሽሎ ያቀረበውን የሲቢኢ ብር መተግበሪያ በሐምሌ 18 ቀን 2016 ዓ.ም በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት የመሰብሰቢያ ማዕከል በይፋ ሥራ ሲያስጀምር የሲቢኢ ብር ተጠቃሚዎች ቁጥር ከ11.7 ሚሊዮን በላይ አድርሶ ነው፡፡

25 Jul 2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት ናዳ ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችን የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በጤናው ዘርፍ ߹ በትምህርት߹ በአካባቢ ጥበቃ፣ በአረንጓዴ ልማት፣ በሰብአዊ ሥራ ድጋፍ እና በሌሎችም ዘርፎች ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ባለፉት አምስት ዓመታት ከ3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል፡፡

24 Jul 2024

አቶ አቤ ሳኖ የ2016 ዓ.ም የአቢሲኒያ የኢንዱስትሪ ሽልማት የዳይመንድ ደረጃ ኒሻን እና ልዩ ዋንጫ ተረከቡ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ለባንኩ ትርፋማነትና ስኬታማነት ባሳዩት ብቃት ያለው አመራር የ2016 ዓ.ም. የዳይመንድ ደረጃ ኒሻን እና ዕውቅና ተበርክቶላቸዋል፡፡ በሽልማት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ በመገኘት ዕውቅናውንና ሽልማቱን የተረከቡት የባንኩ የሰው ኃይል ም/ፕሬዚዳንት አቶ ኤፍሬም መኩሪያ እና ሌሎችም የባንኩ ኃላፊዎች በፕሬዚዳንቱ ቢሮ በመገኘት ሽልማቱን ለአቶ አቤ ሳኖ አስረክበዋቸዋል፡፡