04 Jan 2025
የባንካችን ደንበኞች ብቻ ሳትሆኑ ቤተሰብም በመሆናችሁ ስለአገልግሎት አሰጣጣችን የምትሰጡንን ሀሳብ እና አስተያየት አክብረን እንቀበላልን፡፡ ለተግባራዊነቱም አበክረን እንሠራለን፡፡ የሚያጋጥሙንን ተግዳሮቶች ከናንተ ከደንበኞቻችን ጋር በመሆን ወደምቹ አጋጣሚ እየቀየርን እድገታችንን እናስቀጥላለን፡፡
04 Jan 2025
የኢፌዲሪ የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር እና የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ አህመድ ሽዴ፣ ባንኩ ፈተናዎችን አልፎ ዛሬ ለደረሰበት ስኬት የደንበኞች አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው፣ “እምነታችሁን ስለሰጣችሁን እና ከባንካችን ጋር ስለምትሠሩ እናመሰግናለን’’ በማለት ለባንኩ ደንበኞች መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
27 Dec 2024
እስከ ገና ዋዜማ ድረስ በሚቆየው የሲቢኢ ብር ፕላስ ገና ባዛር ከ400 በላይ የንግድ ድርጅቶችና እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እየተሳተፉበት ይገኛል፡፡
23 Dec 2024
በኢትዮጵያውያን ሥራ ፈጣሪዎች የበለፀገው ይህ የገንዘብ መላኪያ መተግበሪያ ከውጭ ሀገራት በማንኛውም ቦታ እና ሰዓት በፍጥነት በአንድ ጊዜ እስከ 10 ሺ ዶላር ወደ ተጠቃሚ ሂሳብ በነፃ መላክ የሚያስችል እንደሆነ የፋስት ፔይ መስራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ፍፁም ተስፋዬ በሥነ ሥርዓቱ ላይ ተናግረዋል፡፡