News Archive

23 Dec 2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የአዳማ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት በጋራ መሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ይህ ስምምነት በአዳማ ከተማ የሚገኙ ደንበኞች ወርሀዊ የውሀ ፍጆታ ክያቸውን በሲቢኢ ብር ለመፈፀም የሚያስችላቸው ሲሆን፣ ይህም በከተማው ዲጂታል የክፍያ ሥርዓትን ለማስፋፋት የተያዘው ዕቅድ አካል መሆኑ ተገልጿል።

23 Dec 2024

በአሶሳ ከተማ እና አካባቢው ከሚገኙ የሲቢኢ ኑር ደንበኞች ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡

ባንኩ የሚሰጠው ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሸሪዓ መርሆዎችን የተከተለ ስለመሆኑ በማብራሪያ ወቅት የተገለፀ ሲሆን፣ የብድር አገልግሎትን ጨምሮ ደንበኞች ያነሷቸው ሌሎች ጉዳዮች በባንኩ አሠራር መሠረት ምላሽ እንደሚያገኙ ተብራርቷል፡፡

13 Dec 2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በጋራ መሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት የተፈረመው ይህ ስምምነት 26 የሚሆኑ የፌዴራል የመንግስት መሥሪያ ቤቶች እና በስራቸው የሚገኙ 360 ተቋማት ለተገልገዮች የሚሰጧቸው አገለግሎቶችን ክፍያ በዲጂታል አማራጭ የሚቀበሉበትን መንገድ ያመቻቸ መሆኑ ተገልጿል፡፡

13 Dec 2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲቢኢ ኑር ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቱን አስመልክቶ በሠመራ ከተማ የውይይትና የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ-ግብር አከናወነ።

የአል ሃምዱ የሲቢኢ ኑር ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ቅርንጫፍም ተመርቆ ሥራ ጀምሯል፡፡