የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኞች ስጋት ሊገባቸው እንደማይገባ ገለፀ፡፡

መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከሲስተም ማሻሻያ ትግበራ ጋር በተያያዘ በተፈጠረው ችግር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ደንበኞች ስጋት ላይ የሚጥል ክስተት እንዳልተፈጠረ ተገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አቶ አቤ ሳኖ እንደገለፁት በወቅቱ በተከሰተው ችግር የባንኩ ደንበኞች ሂሳብ ላይ ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰም፡፡ አቶ አቤ ባንኩ እድርጎት በነበረ የሲስተም ማሻሻያ ክፍተት ምክንያት መጋቢት 7 ከሌሊቱ ጀምሮ ለተወሰኑ ሰዓታት የቆየ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር የነበረ ቢሆንም ከሌሎች የባንኩ ደንበኞች ሂሳብ ጋር እንደማይገናኝ ገልፀዋል፡፡ ችግሩ በተከሰተበት ሰዓት ውስጥ ከ490 ሺ በላይ የገንዘብ ዝውውር እንደነበረ የገለፁት አቶ አቤ፣ በወቅቱ በዝውውር ውስጥ የተሳተፉ ሂሳቦችን በማገድ በባንኩ ላይ ሊደርስ የነበረውን ጉዳት መቀነስ እንደተቻለ አቶ አቤ ገልፀዋል፡፡ ባንኩ በአሁኑ ጊዜ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውሮችን ለይቶ የጨረሰ ሲሆን፣ ከሌሎች ባንኮች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ቀጣይ ሥራዎችን በመሥራት ላይ እንደሚገኝ አቶ አቤ ገልፀዋል፡፡ ከኤቲኤም በህገወጥ መንገድ ገንዘብ ያወጡ ግለሰቦች በፈቃደኝነት ገንዘቡን እየመለሱ መሆኑን አቶ አቤ ገልፀው፣ ፈቃደኛ በማይሆኑት ላይ ከሚመለከተው የህግ አካል ጋር በመተባበር ገንዘቡ ተመላሽ እንደሚደረግ አስረድተዋል፡፡ ከባንኩ በህገወጥ መንገድ የወጣው ጥሬ ገንዘብ መጠን የማጣራት ሥራ እየተሠራ.. ለተጨማሪ https://www.facebook.com/photo/?fbid=805559308269984&set=pcb.805559418269973