News Archive

07 May 2025

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖን ጎበኙ፡፡

አቶ አቤ በፓናል ውይይቱ ላይ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት በተለይ ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ጋር ተያይዞ በከፍተኛ ሁኔታ መሻሻሉን እንዲሁም ከፍተኛ ብድር በተመጣኝ የወለድ ምጣኔ ለረጅም ጊዜ ብድር ከ16.5 ፐርሰንት በማይበልጥ ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ባንኩ እያቀረበ እንደሚገኝም ጨምረው ገልጸዋል።

29 Apr 2025

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠንካራ የሳይበር ደህንነት ሥርዓት መዘርጋቱን አስታወቀ፡፡

በየቀኑ በርካታ የሳይበር ጥቃቶች ባንኩ ላይ እንደሚሞከሩ የገለፁት አቶ አቤ፣ በባንኩ የተዘረጋው ሲስተም በአግባቡ የሚከላከል እና ሥርዓቱን ሰብሮ ለመግባት የሚፈልግ የትኛውም አጥቂ አልፎ መሔድ የማይችለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

29 Apr 2025

በሲቢኢ በጄ (CBEBeje) የአነስተኛ ብድር እና ቁጠባ አገልግሎት ላይ የግንዛቤ መስጫ መድረክ ተካሄደ፡፡

ሲቢኢ በጄ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የፋይናንስ ተደራሽነትን ለማስፋት በሚያደርገው ጥረት በዲጂታል አማራጭ ለደንበኞች ብድር ለማቅረብ የተዘጋጀ አገልግሎት መሆኑን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሆልሴል ባንኪንግ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ቦኩ ቤኛ ተናግረዋል።

26 Apr 2025

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኮምፕሊያንስ ቀንን ለ4ኛ ጊዜ አከበረ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንቦችን እና መመሪያዎችን አክብሮ የመሥራት (Compliance) ቀን ዘንድሮ ለ4ኛ ጊዜ በማክበር ላይ ያለው “The Future of KYC: Powered by Innovation” በሚል መሪ ቃል ነው።