News Archive

30 Mar 2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምስጋና አቀረበ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ ባንኩ ከሰሞኑ ገጥሞት ከነበረ ችግር ጋር በተያያዘ ለባንኩ ድጋፍ ላደረጉ አካለት በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

30 Mar 2024

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገለፀ፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ፕሮፌሰር መሐመድ አብዱ እንዳሉት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሀገር የልማት እንቅስቃሴ ከፍተኛ እገዛ እያደረገ ያለ ባንክ ነው፡፡ባንኩ በሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ ውስጥ የሚጠብቀበትን እየተወጣ እንዲቀጥል እና በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን ያስቀመጠውን ግብ ለማሳካት ይረዳው ዘንድ ደግሞ የባለድርሻ አካላት የፖሊሲን ጨምሮ ተገቢውን ድጋፍ ሊያደርጉለት እንደሚገባ ዋና ሰብሳቢው አሳስበው፣ ቋሚ ኮሚቴው አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል፡፡

30 Mar 2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያላግባብ ተወስዶ ያልተመለሰውን ቀሪ ገንዘብ ለማስመለሰ ወደቀጣይ እርምጃዎች እንደሚገባ ገለፀ፡፡

በዛሬው እለት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ እንደገለፁት ባንኩ መጋቢት 6፣ 2016 ዓ.ም ሌሊት በተፈጠረ ችግር ምክንያት አላግባብ ከተወሰደበት 801,417,747.81 ብር ውስጥ 622.9 ሚሊዮን ብር (78 በመቶ) እስካሁን የተመለሰ ሲሆን ብር 168,609,283.7 ለመመለስ ቃል ተገብቷል፡፡ አቶ አቤ አላግባብ በ567 ግለሰቦች የተወሰደውን ቀሪ ብር 9,838,329.12 ለማስመለሰ ባንኩ ወደቀጣይ እርምጃዎች እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

26 Mar 2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 622.9 ሚሊዮን ብር (78 በመቶ) ማስመለስ መቻሉን ገለጸ፡፡

ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ መጋቢት 6፣ 2016 ዓ.ም ሌሊት በተፈጠረ ችግር ምክንያት 801,417,747.81 ብር ያላግባብ ተወስዶ እንደነበር ባንኩ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ያሳወቀ ሲሆን፣ 622.9 ሚሊዮን ብር ማስመለስ መቻሉ ተገልጿል፡፡ ከባንኩ አላግባብ የተወሰደውን ገንዘብ ለማስመለሰ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ለህብረተሰቡ ለማሳወቅ በተዘጋጀው በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ እንደገለፁት ችግሩ በተከሰተበት ቀን ከምሽቱ 3፡38 ጀምሮ እስከ ሌሊቱ 8፡45 ድረስ በ25,761 ሂሳቦች አማካኝነት 238‚293 ህገወጥ ግብይቶች ተከናውነዋል፡፡