News Archive

28 Oct 2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ሀይብሪድ ዲዛይን ኅ.የተ.የግ.ማ (ራይድ ትራንስፖርት) በተለያዩ ዘርፎች በጋራ መሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የራይድ ትራንስፖርት ተጠቃሚ ደንበኞችን በባንኩ ዲጂታል የክፍያ አማራጮች ክፍያቸውን መፈፀም ለማስቻል፣ ራይድ በሚያቀርባቸው የተለያዩ ዲጂታል ፕላትፎርሞች ላይ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ በጋራ ለመሥራት፣ ለኤሌክትሪክ መኪኖች ግዥ የፋይናንስ አገልግሎት ለማቅረብ እንዲሁም በቀጣይ በሌሎች ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ስምምነት ነው፡፡

14 Oct 2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በግብር ከፋዮች ሽልማት የፕላቲኒየም ደረጃና ልዩ ተሸላሚ ሆነ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሽልማት መርሐ ግብሩ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ ሆኖ የቆየ ሲሆን በዚህኛው ዙር ከፕላቲኒየም በተጨማሪ ልዩ ተሸላሚም ሆኗል፡፡

21 Sep 2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ቪዛ ኢንተርናሽናል አጋርነታቸውን ወደ ላቀ ደረጃ በማድረስ በጋራ ለመስራት ተስማሙ፡፡

ቪዛ ኢንተርናሽናል እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያደረጉት ስምምነት ለአምስት ዓመታት የሚቆይ ሲሆን፤ ቪዛ ካርድን በብዛት ለ ኢ.ን.ባ ደንበኞች ለማቅረብ እና ለባንኩ ሠራተኞች የአቅም ግንባታ ሥልጠና ለመስጠት እንደሚያስችል ለማወቅ ተችሏል

12 Sep 2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የስፖርት ማኅበር በዓመቱ ያገኛቸውን ከ40 በላይ ዋንጫዎች ለባንኩ አስረከበ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን ለመጀመሪያ ጊዜ ያሳካው የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ፣ ለ7 ዓመታት የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮኑ የሴቶች ቡድን በሴካፋ ሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊ መሆኑና ኢትዮጵያን በመወከል በፓሪስ ኦሎምፒክ 2024 የተሳተፈችው የባንኩ አትሌት ፅጌ ዱጉማ የብር ሜዳሊያ ማምጣት መቻሏ ዓመቱን ልዩ እንደሚያደርገው አቶ ኤፍሬም ተናግረዋል፡፡