የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በመገኘት ኤክስፖው በይፋ መከፈቱን አብስረዋል፡፡

አቶ አቤ ሲቢኢ ብር ፕላስ በዲጂታል የገንዘብ እንቅስቃሴ ውስጥ ይዞ የመጣውን በርካታ አዳዲስ ነገሮች ምክንያት በማድረግ ኤክስፖው ‘አዲስ ነገር በአዲስ ዓመት’ የሚል መሪ ቃል እንደተሰጠው ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን በማድረግ ሂደት የመሪነት ድርሻውን እየተወጣ እንደሚገኝ አቶ አቤ በዚሁ ጊዜ አመልክተዋል፡፡ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እየተፈፀመ ከሚገኘው የገንዘብ ግብይት ውስጥ ከ ከ76 እስከ 78 በመቶ የሚሆነው በዲጂታል አገልግሎቶች እንደሚፈፀም ነው አቶ አቤ የተናገሩት፡፡ ከ8 ዓመታት በፊት የተጀመረው የሲቢኢ ብር አገልግሎት ከባንኩ ዲጂታል የክፍያ አማራጮች መካከል አንዱ መሆኑን የገለፁት አቶ አቤ፣ ተሻሽሎ በአዲስ መልክ የቀረበው የሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያ ለአጠቃቀም ምቹ እና በርካታ አዳዲስ ነገሮችን ያካተተ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ አቶ አቤ ደንበኞች ሲቢኢ ብር ፕላስን በመጠቀም ህይወታቸውን ቀላል ማድረግ እንደሚችሉ ገልፀው፣ በሲቢአ ብር ፕላስ የኤግዚቢሽኑን መግቢያ ትኬት በመቁረጥ እና በመገበያየትም መኪናን ጨምሮ ባንኩ ያዘጋጃቸው በርካታ ሽልማቶችን ማሸነፍ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ አቶ አቤ የ2017 አዲስ ዓመት መልካም ምኞታቸውን ከወዲሁ አቅርበዋል፡፡ በታላቁ ‘ሲቢኢ ብር ፕላስ ኤክስፖ 2017’ የአዲስ ዓመት ዋዜማ ኤግዚቢሽን እና ባዛር ይፋዊ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት በርካታ እንግዶች ተገኘተዋል፡፡