የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ሲቀበል የሚያሳይ ምስል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን፡፡ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን በ 30 ጨዋታዎች 64 ነጥብ እና 57 ጎሎችን ከመረብ አሳርፏል። ከተቆጠሩት ጎሎች መካከል ግማሽ የሚሆኑት 28 ጎሎች የተቆጠሩት በ3 ተጫዋቾች (አዲስ ግደይ 12፤ ሳይመን ፒተር 9፤ ባሲር ሁመር 7) ነው። ይህም ባማካኝ ወደ ሁለት ጎል የሚጠጋ በያንዳንዱ ጨዋታ በማስቆጠር የሊጉ ድምቀት ነበር።