በጉጉት የሚጠበቀው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጨረሻ ጨዋታ ጀመረ!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ፣የባንኩ የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች እንዲሁም በርካታ የክለባችን ደጋፊዎች በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተዘጋጀላቸውን የክብር ቦታ ተቀምጠው ጨዋታውን አየተከታተሉ ነው፡፡ ጨዋታው በተጀመረ 03' ደቂቃ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሱሌይማን ሀሚድ አማካኝነት የመጀመሪያውን ጎል አስቆጥሯል። ጨዋታው በተጀመረ 34' ደቂቃ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዲስ ግደይ አማካኝነት ሁለተኛውን ጎል አስቆጥሯል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን የመጨረሻ ጨዋታውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 2 ለ መድህን 0 በሆነ ውጤት ተጠናቋል! የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን በ 30 ጨዋታዎች 64 ነጥብ በመሰቡሰቡ በአጠቃላይ 57 ጎሎችን ከመረብ በማሳረፍ ሰኔ 29 ቀን 2016 ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን አሸናፊ ሆኗል፡፡ አዲስ ታሪክ በደማቅ ቀለም ! የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!