የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ የዛሬን ጨዋታ ለመታደም ሀዋሳ ገቡ።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ የሚመራ የልኡካን ቡድን ጨዋታውን ለማድመቅ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወንዶች እግር ኳስ ቡድንን ለመደገፍ ሀዋሳ ገብቷል። የልዑካን ቡድኑ በሀዋሳ አየር ማረፊያ ሲደርስ በርካታ የክለቡ ደጋፊዎች እንዲሁም የባንኩ የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች አቀባበል አድርገውላቸዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን ዛሬ ለዋንጫ በ10፡00 ሰዓት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ከኢትዮጵያ መድን ጋር ወሳኝ ጨዋታ ያደርጋል። ውጤቱን እየተከታተልን እናቀርባለን። መልካም ዕድል ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን!