የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከምስራቅ አፍሪካ ባንኮች በ3ኛ ደረጃ ተቀመጠ፡፡

አፍሪካን ቢዝነስ ባወጣው መረጃ መሰረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2022 ባስመዘገበው አፈፃፀም በ929 ሚሊዮን ዶላር ካፒታል ከምስራቅ አፍሪካ ባንኮች መካከል በ3ኛ ደረጃ ተቀምጧል፡፡ የኬኒያዎቹ Equity Bank Group (1,558 ሚሊዮን ዶላር ካፒታል) እና KCB Bank (1,233 ሚሊዮን ዶላር ካፒታል) የመጀመሪያውን እና ተከታዩን ስፍራ ይዘዋል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 22 ቢሊዮን ዶላር ጠቅላላ ሀብት በማስመዝገብ ከሁሉም የምስራቅ አፍሪካ ባንኮች ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዝ ሲሆን፣ ከEquity Bank Group እጥፍ የሚጠጋ ኃብት እንዳለው አፍሪካን ቢዝነስ በሪፖርቱ ጠቅሷል።