በሲቢኢ ብር መተግበሪያ ‘Market Place’ የዲጂታል ትኬት ሽያጭ አገልግሎት መስጠት ተጀመረ!

ከነሀሴ 14 - ጳጉሜን 5 ቀን 2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማእከል የሚካሄደው የአዲስ አመት ኤግዚቢሽን እና ባዛር ተሳታፊዎች የሲቢኢ ብር መተግበሪያ ‘Market Place’ አገልግሎትን በመጠቀም ባሉበት ቦታ ሆነው የመግቢያ ትኬት መቁረጥ የሚያስችል አገልግሎት መስጠት ተጀመረ። ኤግዚቢሽን እና ባዛር፣ ኮንሰርት፣ የጥበብ ምሽቶችና የመሳሰሉ ሁነት አዘጋጆች ወደ ባንካችን በመምጣትና የሲቢኢ ብር ‘Market Place’ ተጠቃሚ በመሆን የመግቢያ ትኬት ሽያጫቸውን ቀላል እና ተደራሽ ማድረግ ይችላሉ፡፡ የሲቢኢ ብር መተገበሪያን ለማውረድ፡ • ለአንድሮይድ ስልኮች፡- https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr • ለአይፎን ስልኮች፡- https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787