ባጠናቀቅነው የ2024/25 በጀት ዓመት በፈረንጆቹ ጁን ወር መጨረሻ፤ ባንካችን ከ515 ቢሊየን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ የማሰባሰብ ተግባር በማሳካቱ የተሰማኝን ከፍ ያለ ደስታ ልገልጽላችሁ እወዳለሁ፡፡ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ በባንካችን የተመዘገበ አዲስ ታሪክ ነው፡፡ ለዚሁ ታላቅ ስኬት አሻራችሁን ላኖራችሁ ሁሉ እንኳን ደሰ አላችሁ እላለሁ፡፡
አቶ ኃይለየሱስ የደንበኞች አገልግሎት ወር በተለያዩ ዝግጅቶች መከበሩን አስታውሰው፣ ሁነቱ ባንኩ ከደንበኞቹ ጋር ይበልጥ የተቀራረበበት፣ ለደንበኞች ያለውን ክብር የገለፀበት እና በቀጣይ ሊያሻሽላቸው ስለሚገቡ ጉዳዮችም ግብአት ያገኘበት መሆኑንም ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አትሌቲክስ ቡድንለሽልማት ከተዘጋጁ ሦስት ዋንጫዎች ሁለቱን ያሸነፈ ሲሆን፣ 12 የወርቅ ፣11 የብር እና 13 የነሀስ ሜዳሊያዎች በማምጣት ከፍተኛ ድል መቀዳጀት ተችሏል፡፡