ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ ዛሬ ከሌሊቱ 07፡00 ሰዓት እስከ ነገ ጠዋት 12፡00 ሰዓት ድረስ ሁሉም የባንካችን ዲጂታል የክፍያ አማራጮች አገልግሎት በጊዜያዊነት ይቋረጣሉ። በመሆኑም ክቡራን ደንበኞቻችን ይህን አውቃችሁ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ እየጠየቅን፣ ለሚፈጠረው የአገልግሎት መስተጓጎል ይቅርታ እንጠይቃለን።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም. በውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓት ላይ ማሻሻያ ማድረጉ ይታወሣል፡፡ ይህ ለውጥ ኢትዮጵያን ተወዳዳሪ ወደሆነና በገበያ ላይ ወደተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ሥርዓት እንደሚያሸጋግራት የታመነበት ሲሆን ይህንኑ ለማስፈጸም አዲስ የውጭ ምንዛሪ መመሪያ ተዘጋጅቶ በሥራ ላይ ውሏል፡፡ ይኸውም ባንኮች የውጭ ምንዛሪ ገቢያቸውን ለማሣደግ የሚረዳ ሲሆን ከገበያዉ ላይ የውጭ ምንዛሪ ተወዳድረው እንዲገዙ ያግዛል፡፡ ቀደም ብሎም ባንኮች የውጭ ምንዛሪ ለደንበኞቻቸው የሚደለድሉበት የቀድሞው አሠራር የተሻረ በመሆኑ ለደንበኞች ጥያቄ ቶሎ ምላሽ ለመስጠትና የውጭ ምንዛሪ አቅርቦትን ቀልጣፋ ለማድረግ አስቻይ ሁኔታ ፈጥሯል፡፡ ባንካችንም አዲሱ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ማሻሻያ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ የውጭ ምንዛሪ ምንጩን ለማሣደግ በገበያው ላይ ተወዳዳሪ የምጣኔ ተመን በመስጠት እየሠራ ሲሆን የውጭ ምንዛሪ ለደንበኞች በመስጠት የውጪ ገቢ ንግድ የተቀላጠፈ እንዲሆን አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል፡፡ በዚህም መሠረት ከሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም. እስከ መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ በአራት ዙር የአሜሪካን ዶላር 282,459,436.76 ለበርካታ ደንበኞች መደልደል ችሏል፡፡ የውጭ ምንዛሪ ፍቃድ የተሠጣቸው ደንበኞች በተለያየ የሥራ ዘርፍ ላይ ያሉ ሲሆን ፋብሪካዎች፤ የገቢ እና ወጪ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፡ መድኃኒት አምራቾች፤ አገልግሎት ሰጪዎች፤ የመንግስትና ሕዝብ ተቋማት እና በውጭ ኢንቨስትመንት የተቋቋሙ ድርጅቶች ይገኙበታል፡፡ ከዚህም ውስጥ፤ ለፋብሪካ ጥሬ እቃ እና ለተጠቃሚ የሚቀርቡ የተለያዩ የምግብ፤ መድኃኒት እና መገልገያ ቁሣቁሶች መግዣ------------------- የአሜሪካን ዶላር 208,290,167.10 ለማሽነሪዎች መግዣ-------------------------------------- የአሜሪካን ዶላር 42,777,753.94 ለመለዋወጫ መግዣ ------------------------------------- የአሜሪካን ዶላር 18,153,777.53 ለአገልግሎትና የተለያዩ ክፍያዎች -------------------------- የአሜሪካን ዶላር 13,237,737.99 በአጠቃላይ የአሜሪካን ዶላር 282,459,436.76 የተደለደለ ሲሆን ደንበኞች አጠቃቀማቸዉ አዝጋሚ ቢሆንም የተፈቀደላቸውን የውጭ ምንዛሪ በመጠቀም ላይ ይገኛሉ፡፡ እስከ አሁን ያለዉ አማካይ አጠቃቀምም 28% ብቻ ነዉ፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለክቡራን ደንበኞቹ ማረጋገጥ የሚፈልገው የውጭ ምንዛሪ ድልደላን የውጭ ምንዛሪ ፍላጎት ለሚኖራቸው ሥራዎች ሁሉ ቀጣይነት ባለው መልኩ በመደበኛነት የሚያከናውን መሆኑን እየገለፀ አዲሱ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ፖሊሲ ለባንኮች አዋጭነትን ባገናዘበ መልክ ድልደላ እንዲያካሂዱ መፍቀዱ ቀድሞ የነበረውን ሁኔታ መቀየር ማስቻሉን ለማስገንዘብ እንወዳለን፡፡
መንግስት በቅርቡ ባወጣው አዲስ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሕግ ቁጥር 1341/2016 መሰረት ባንኮች በሚሰጧቸው አገልግሎቶች ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲጣል ስለታወጀ ባንካችንም ይህንን የተጣለውን ግዴታ ለመወጣት ከመስከረም 21 ቀን 2017 ዓ. ም ጀምሮ በባንካችን አገልግሎቶች ላይ በሚከፈል የአገልግሎት ክፍያ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ታሪፍ የተጨመረ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን።
በአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ ሁለተኛ ዙር ቅድመ ማጣርያ የመጀመሪያ ጨዋታ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በታንዛኒያው ያንግ አፍሪካንስ 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት ተሸንፏል፡፡ የመልስ ጨዋታው በቀጣዩ ቅዳሜ ዛንዚባር ላይ የሚደረግ ይሆናል።
በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ኢትዮጵያን የወከለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ መስከረም 4 ቀን 2017 ዓ/ም ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት በአበበ ቢቄላ ስታዲየም ከታንዛኒያው ያንግ አፍሪካንስ ጋር ይጫወታል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በካፍ ሻምፒየንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ የዩጋንዳውን ኤስ ሲ ቪላ በድምር ውጤት 3 ለ 2 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉ ይታወቃል። መልካም ዕድል ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን!
CBE Noor is one of the full-fledged interest free banking services. Designed to comply with the central tenets of Sharia (or Islamic law) of doing business.
The core processes of the bank entrusted with the task of international banking services. The services are now provided at all branches of the bank with a single contact point of customer service relationship officers assigned for this purpose only.
Delivering banking services through high level of process automated machines and web-based. It provides easy, convenient, flexible and secure banking services for CBE customers using their digital cards, mobile phone, or internet accesses.
ቪዛ ኢንተርናሽናል እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያደረጉት ስምምነት ለአምስት ዓመታት የሚቆይ ሲሆን፤ ቪዛ ካርድን በብዛት ለ ኢ.ን.ባ ደንበኞች ለማቅረብ እና ለባንኩ ሠራተኞች የአቅም ግንባታ ሥልጠና ለመስጠት እንደሚያስችል ለማወቅ ተችሏል
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን ለመጀመሪያ ጊዜ ያሳካው የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ፣ ለ7 ዓመታት የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮኑ የሴቶች ቡድን በሴካፋ ሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊ መሆኑና ኢትዮጵያን በመወከል በፓሪስ ኦሎምፒክ 2024 የተሳተፈችው የባንኩ አትሌት ፅጌ ዱጉማ የብር ሜዳሊያ ማምጣት መቻሏ ዓመቱን ልዩ እንደሚያደርገው አቶ ኤፍሬም ተናግረዋል፡፡
አቶ አቤ ማእከሉ ከ7 ሺ 500 በላይ የሀገር ባለውለታ አረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማንን ከወደቁበት አንስቶ መጠለያ በመስጠት እና በመንከባከብ እየሠራ ያለው ሥራ ሊመሰገን እና ሊደገፍ የሚገባው መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሻምፒዮን ሆኗል! የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኬኒያ ፖሊስ ቡሌትስን 1 ለ 0 በማሸነፍ የካፍ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የሴካፋ ሀገራት ሻምፒዮን ሆኗል!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኬኒያው ኬኒያ ፖሊስ ቡሌትስ ሐሙስ ነሀሴ 23 ቀን 2016 ዓ/ም በአበበ በቂላ ስታዲየም በሚደረገው ፍፃሜ ጨዋታ ተፋላሚዎች ናቸው፡፡
ኤክስፖው ስያሜውን ያገኘበት የሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያ ለአጠቃቅም ይበልጥ ምቹና የተለያዩ አማራጮችን የያዘ መሆኑን የገለፁት አቶ አቤ፣ ሕብረተሰቡ ይህንኑ አገልግሎት እንዲጠቀም አበረታተዋል ።
Branchs
Customers
Partners
Transactions per Month